የኢትዮጵያውያን ቅምር
ጥልቅ ረጅም ባለስር።
ግንደ ትልቅ ምርጥ ዛፍ
ጥላው ሰፊ የሚተርፍ
መከራ ችግር ብዙ ግፍ
ሲፈራረቁ በየ ሰልፍ
ለብዙ ጊዜ ያለማረፍ
የደርስንበት ጠንካራው ክንፍ
እንዳይደክምብን ብሎ ስንፍ
አይዞን በማለት ሞራል ድጋፍ
እንስጠው ቶሎ በመጣደፍ።
ዝም ብሎ ማየት
ዋ! የለውም ውጤት።
የኢትዮጵያ ነገር
ያሳስባል ከምር።
ከአሁኑ ከአልተለፋ ከአልተሰራ
ኢትዮጵያን ለማውጣት ከመከራ
ከአልተወጣን የእኛን አደራ
እንዳይሆን ባዶ ፉከራ።
ስለዚህ፣ የኢትዮጵያዉያን ክር
ሳይበጠስ እንዲኖር
ከልብ ይሰለፍ ሁሉም ያብር
በመቀባበል የመጠበቂያዉን በትር
ኢትዮጵያም ለዘላለም እንድትኖር።
