The Patriotic And Heroic Ethiopians! አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ጀግኖች ኢትዮጵያን ጠብቀው ለትውልድ አስረክበዋል! እኛስ?

Sunday, April 20, 2014
ኢትዮጵያን ጠብቅ!
ኢትዮጵያ እንዳጠፋ
በአንድነቱ ግፋ
በውሸት በወሬ ይቅር አትገፋ
አትተኛ በቁምህ ተው አታንቀላፋ።
ሕዝብህ ሲቸገር መሬትህ ሲሸጥ
እንዲህ ተበትነህ ከምትቀመጥ
አንድነቱን ፈጥረህ ጠላት አንቀጥቅጥ።
ይሄው ተለያይተህ እየተናቆርህ
አገርህን ለቻይና ለሕንድ አስረከብህ።
ተው አንተ ሰው ንቃ
በሆነው ባልሆነው ይብቃህ አትጠቃ።
በዋናው ጠላት ላይ ጠንክር አተኩር
አጥፋ ሚለየውን በጎሳ በዘር።
ከመፃፉ ሁሉ የመጣን ታሪክ
እንዴት በኛ ጊዜ ይውረሰው እከክ።
በሩቅ የሚለየው ልዩ ቀለምህ
ኢትዮጵያውይነት ነው መስመር ሐረግህ
ችግሩን ፍታና በጋራ ቁመህ
የጥላቻን መርዝ ጠርገህ አፅድተህ
ጠላቶችን ሁሉ ከአገር አውጥተህ
ዓለምን ጉድ አሰኝ በአንድ ላይ ሁነህ።