አለን ቁመናል ልጆቺሺ
እንዳይጠፋ ክቡር ገፅሺ
በመመከት ከጠላትሺ
ከሚጥሩት ሊበትኑሺ
አከላትሽን ከሚቆርጡሺ
ከተገዙት ለሹምባሺ
አባቶች እንዳቆዩሺ
ገድለውና ሙተውልሺ
ከትውልድ ትውልድ እዳዳኑሺ
እኛም አንሁንም ተውቃሺ
እንሆናለን ፈጥኖ ደራሺ
አምላክን ይዘን በዙሪያሺ
እንታገላለን ልናቆይሺ
ዘላለማዊ ህይወት እንዲኖርሺ
ኢትዮጵያ ወይንም ሞት ብለንልሺ
መክትና ድረስ ፈጥረንልሺ
ተነሳን ልጆችሺ፣ ተነሳን ልጆችሺ።
