ሞረሽ ወገኔ የቅሌት ፖለቲካ ኢትዮጵያዊነትን ተቃውሞ
እንደ ወያኔ ጎጠኝነትን እያራመደ ነው።
ከቀመሩ ደሳለኝ
ወያኔ /ሕወሓት በፀረ_ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያዊነትና በሰንደቅ ዓላማችን በዋና ጠላትነት ሲነሳ ለዚህ
መሰረትና ዋና አውታር የሆኑትን የአማራውን ማኅበረሰብና የክርስትና ሃይማኖቱን ማጥፋት ወይንም
መጠቀሚያ ማድረግ፣ አገሪቱን በቋንቋ ከፋፍሎ በማዳከም ተገዥና ታዛዝ አድርጐ ሃብት ንብረቷን
በመዝረፍና በመሸጥ` ለረዥም ጊዜ ሕዝቧን ማሰቃየት፣ማደህየትና መግደል ታስቦና ዓላማ ተደርጐ ነው።
የዚህን ጠባብ፣ጎጠኛ፣ከሃዲ፣ውሸታም ሌባና ዘራፊ፣ ማፊያ አጋሚዶ ባንዳ የቀየሰውን የተንኰል ጠማማና
ወልጋዳ፣ አጥፊና የአናሳ ሴራ፣ የፀረ_ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት መንገድ ተከትሎ በብሔር አማራው
መደራጀት አለበት ማለትና "የነፈሰበት ኢትዮጵዊነት" ብሎ የአማራውን ማኅበረሰብ አጥቦና አሳንሶ ከማየት
በአሻገር ወያኔ ጠላት አድርጐና በመፍራትም ሊያጠፋና ሊያዳክም ያለመውና ያቀደው በኢትዮጵያዊነት
ላይ ሲሆን ሞረሽ ወገኔም ያለመው ኢትዮጵያዊነትን አውልቆ መጣል ነው።
ሞረሽ ወገኔ ኢትዮጵያዊነትን ከአማራውና ከሌላው ኢትዮጵያዊ ሁሉ በመንጠቅና ለማስቀረት የነፈሰበት
ብሎ ማራከስ የለየነት ጠላትነት፣ሽፍጥና የለበጣ አቋም ነው።ሞረሽ ወገኔ ኢትዮጵያዊነትን ሲቃወም
እንድህ ይላል "የአማራው ሕዝብ የኢትዮጵያዊነቱን እምነት አውልቆ ጥሎ እንደሌሎቹ ብሔርተኞች
ብሔተርኛ ካልሆነ እንደ ወልቃይት ሕዝብ ይጠፋል" በማለት አማራን ትንሽና ውስን፣ ጠባብና ጎጠኛ
አድርጐ በወያኔ መንገድ ለወያኔ አላማና ስልት ተባባሪነቱን እያራመደ ነው ብል ሃቅነቱ ደጋግመው በመጻፍ
በድፍረት በዓይን አውጣነት ለማሳየት መሞከሩ መረጃው ነው።በሌላ ጊዜ ደግሞ በዚያው አንድ ጽሁፍ
ውስጥ "የአማራው ሕዝብ በኢትዮጵያዊነት ጸንቶና ኮርቶ እስከ መጨረሻው ትግሉን ይቀጥላል" በማለት
ግራ የተጋባ አቋም የለሽ አሰብ ይዞ አንባቢዎችን በማሳሳት የግንቦት 7ን ዓይነት ወያኔዊ አቋሙን
ያራምዳል።
ያውቃል ወይ ይማራል፣ ይረዳል ተብሎ እንጂ
ጥንትም ነፍሰ ገዳይ መሪው ነው ከሃጂ።
ሞረሽ ወገኔ ያልገባው ነገር ይህ ነው።
አማራ፣ የወያኔ የክልል ካርታ እንደ ሚያሳየውና በየሚድያው የተሳሳቱና አሳሳች መረጃዎች እንደሚያሳዮት
ሳይሆን፤በሕዝብ ብዛቱ፣በቆዳ ስፋቱ፣በአሰፋፈሩ መላ_ ኢትዮጵያን ያዳረሰ፣ ከሁሉም በሔረሰቦች ጋር
በደም የተዋሃደ ተዋልዶ የተሳሰረና ሥር የሰደደ ትልቅና ግዙፍ ነው።በኢትዮጵያ ውስጥ ክልል የለውም
በሁሉ ቦታ እንዳሻው ተዘዋውሮ ይኖራል።
ይህ የኢትዮጵያ ሕዝብ ክፍል አርቆ አስተዋይና ታጋሽ ኃይል ከመሆኑ ጋር ኢትዮጵያን፣ኢትዮጵያዊነትንና
ሰንደቅ ዓላማን መለዮና እምነት አድርጐ በፅኑ የቆመ፣የማይበርድ ፣የማይበገር፣ እጅ የማይሰጥ አሸናፊና
ወሳኝ ነው።አማራ እግዚአብሔርን የሚፈራ፣ቸርነቱንና ደግነቱን ያስተዋለ፣ልቦናው ንፁህ የሆነ፣መንፈሳዊ
ጸጋን የተላበሰ፣አብሮ በሰላም መኖርን፣ ፍትህን፣እኩልነትን፣መከባበርን፣የጋራ እድገትን፣ብሔራዊ ብልጽግናን፣የሕግ የበላይነትን ያነገበ፣ለ7 ሺህ ዘመናት በብሔራዊ አንድነት፣ ታሪኩና ነፃነቱ የሚኮራ፣
ደስታና መከራን ከሌላው ጋር እኩል ተካፍሎ የሚኖር ሰላማዊ ሕዝብ ነው።
በዚህ ገርና ሰላማዊ ሕዝብ ላይ በየጊዜውና በየቦታው ዓይነ_ኅሊናቸው የጨለመና የላቀጠ አክራሪ ጠባብ
ጎሰኛ ትዕቢተኞች በድርጅትና በመንግሥት ደረጃ እየተነሱ እጅግ አሰቃቂ ጀኖሳይድ ፈጽመውበታል።ኦነግ፣
ሻቢያ፣ወያኔ፣ደርግና መኢሶን የአማራውን ሕዝብ ንፁህ ደም ያፈሰሱ ወንጀለኞች ሲሆኑ፣ በተለይ ኦነግ፣
ወያኔና ሻቢያ ከመነሻው አጀንዳቸው የተቀረጸው የአማራውን ሕልውና ለማጥፋት ባቀደና ባለመ ጀኖሳይድ
ፕሮግራም በመሆኑ አማራውን በግፍ ፈጅተውታል።በግንቦት 7 ውስጥ የተኰለኰሉት ግለሰቦችና አጋር
ድርጅቶች አሰላለፍና አያያዝ፣ የኢሳት ቴሌቪዥን ማሽንክ ቃለ_ምልልስና የለበጣ ፕሮፓጋንዳ፣የመድረክ
አላቢላዎች ሐኬት አካሄድ ሁሉ አማራውን በፖለቲካ ያገለለና ለሌላም የዘር እልቂት ለመዳረግ በስውር
ያሴረ ፀረ_አማራነት፣ፀረ_ኢትዮጵያ፣ፀረ_ኢትዮጵያዊነትና ፀረ_ስንደቅ ዓላማ ነው።
አማራና ውቅያኖስ ቢጨልፉት_ቢጨልፉት የማያልቅ በሁሉም ኢትዮጵያዊ ደም ውስጥ ያለ ግዙፍ
ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ኃይል በመሆኑ ይህን ሕዝብ መፈታተንና በፖለቲካ ማግለልና ለማጥፋት
ማሰብ ፈንጂ በእራስ ላይ እንደ ማጥመድና እንደ መጫወት ነው።
ይህ በዚህ እንዳለ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊነት ብዙ የተለያዮ ብሔረሰቦች እንዲሁም ግለሰቦች በየጊዜው
ሰለባዎች ሆነዋል።በወያኔ ብዙ የትግራይ ሰዎች ሳይቀሩ በኢትዮጵያዊነት አቋማቸው ተገለዋል፣ታስረዋል
አሁንም እየተፈጸመባቸው ይገኛሉ። የትግራይ ሕዝብም በብሔር ተደራጅቶ በፀረ_ ኢትየጵያዊነት
አልዘመተም። ወያኔ_የማፊያ አጋሚዶው አወ በጠላትነት ለማጥፋት ለመዝረፍ የተሰለፈ ነው።ሌሎች
በኢትዮጵያዊነት እንደ ጋምቤላ፣ አፋርና የደቡብ ሕዝብ በኢትዮጵያዊነት እየተገደሉና እየተንገላቱ ያሉ፣
በጠበቀና በማይወላውል ኢትዮጵያዊነት አቋም እንዲሁም ከአማራው ጋር ጥብቅ ግንኙነት አላቸው።ይህ
መዘንጋት የሌለበት ሃቅ ነው።
ሞረሽ ወገኔ አማራውን በበሄር ማደራጀት የማይችልና ተቀባይነት የሌለው መላ_ቅጡ የጠፋበት በአንድ
ነጠላ የሚመራና በጥቂት አባላት ጥቅም ላይ የተመሰረተ ነው።
ስለዚህ ሞረሽ ወገኔ የነፈሰበት ኢትዮጵያዊነት እያለ ኢትዮጵያዊነትን ከሚኮንንና የብሔር ድርጅትን ለወያኔ
አጋዥ ሆኖ መሰበክ ቅሌት ስለሆነ በአስቸኳይ እንድያቆምና አደብ እንዲገዛ አሳስባለሁ።እንዲሁም አገር
ወዳዱ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ይህን የሞረሽ ወገኔን ፀረ_ኢትዮጵያዊነት እንዲያውቀውና እንዲያወግዘው
ከማሳሰብ ጋር እጠይቃለሁ።ፀረ_ አማራነትን ለመፋረድ፣ለመከላከልና ኢትዮጵያን ለማዳን እያንዳንዱ
ኢትዮጵያዊ ኃላፊነት ስለላለበት ግደታውን አውቆ ሁሉም ለኢትዮጵያ፣ለኢትዮጵያዊነት፣ለሰንደቅ ዓላማና
ለሕግ የበላይነት ዘብ ይቁም።
ምንጊዜም ኢትዮጵያ፣ኢትዮጵያዊነት ድል አድራጊ ነው!!
ኢትዮጵያዊነትና አማራ አንድ ነው!
አማራ ብሄር፣ክልል የለውም !
